በይዘቱ ለአገራችን ለመጀመሪያ የሆነውን የዜጎችን ደህንነትና
መብት ለማስጠበቅ ለማንኛውም ሀይማኖት ክፍል ያልወገነ Ethio-Cult Information Center ወደ
ህይወት መጥራት ያስፈለገበት ምክንያት ከዘመናት ወደ ዘመናት በአምልኮ ስም ተጠቂ የሚሆኑ ወገኖች ችግራቸው በአምልኮ
ስም የሚፈጰምባቸው ወንጀል ህዝብ አንደሌላው አለም የሚያውቅበት መንገድ ባለመኖሩ ተሸፋፍኖ በአምልኮ ስም በመቅረቱ
ብዙዎች ተጠቂ ሲሆኑ ታይተዋል::ኢትዮጵያ
ጎጂ አምልኮ
መከላከያና መረጃ
መዐከል(ኢጎአመ*3 / ECIC)
ይህንን አለማወቅ በህብረተሰባችን ውስጥ ለመግታትና ወንጀል እንጂ
ከአምልኮ ጋር ግንኙነት የሌለው ድርጊት መሆኑን ለማሳየትና የወደፊቱ ትውልድም አምልኮን አንደማስክ እየተጠቀሙ
የተለያዩ ወንጅሎችን በዜጎች ላይ የሚፈጰሙ ድርጅቶችንና አምልኩኝ ባዮቻቸውን ለይቶ አንዲያውቅ መረጃዎችን Ethio-Cult Information
Center ያቀርባል::
ውድ አንባቢያን ግለሰቦችን በአምልኮ መሰል ስም ቀርቦ ጥቂቶችን ከህዝብ
ነጥሎ በ 21ኛው ክፍለ ዘመን በሌላው አለም (International
Standard) ተቀባይነት በሌለው መልኩ በማስቸገርና ብዙዎች ደካማ ዜጎቻችን ከሚደርስባቸው ስቃይ ማለትም
ጤናቸውን On/off አንደሚል መብራት በማሳመምና በተጨባጭ የታየ ደም አስከመትፋት: ሽባ እስከመሆን ድረስ በአምልኮ
ስም ቀርቦ በማሰቃየትና በስራቸውና በትዳራቸው ሰላምን በማሳጣት በምድር ህይወታቸው ተስፋ አስኪቆርጡ ድረስ በማሰቃየት
የሚረዳኝ ዜጋ የለም ብለው ችግራቸውን ለህዝብ መናገር ፈርተው የሚሰቃዩበትንና የምድር ህይወታቸውን አንደሮቦት ዜጎችን
በአምልኮ ስም የመጠቀሚያውን ሲስተም በማጋለጥና ለሌሎች ለትምህርትና ለጥንቃቄ አንዲሆን ላላወቁ ቤተሰቦቸ : ወዳጆችና
ለመገናኛ ብዙሀን (ጋዜጣና መጵሄት ኢንተርኔት የመሳሰሉትን ) በማሳውቁ ይተባበሩን ::
በምአራቡ
አለም አንደዚህ አይነት ድርጊቶች መንግስት በጀት መድቦለት የሚንቀሳቀስ Cult Information Center ለምሳሌ
cultinformation.org የሚያጋልጠው ድርጊት ሲሆን
አገራችን ካላት የአኢኮኖሚ ሁኔታ አርስ በአርሳችን የማያውቁ ወደፊት ሊጠቁ የሚችሉ ዜጎችን በማሳወቅ ለማዳን
አንረዳዳ::
ሌላው ወድ አንባቢያን ሊተባበሩን የሚችሉት ነገር ቢኖር ከዚህ በፊትም ይሁን በቅርቡ
በአካባቢዎት ወይም በመገናኛ ብዙሀን በካሴት : ኢንተርነት ወይም በምስክርነት መልክም ይሁን አርስዎ የሚያውቁት
ተመሳሳይ ድርጊቶች ካሉ በዚህ ፎረም ላይ ቢያወጡት በዝግጅት ላይ ያለው Ethio- Cult Information
Center ሆም ፔጅ ውስጥ ስለሚወጣ ሌሎች የማያውቁን አንዳይታለሉና አንዳይጠቁ ለማሳወቅና ለትምህርት ድርጊቱ ታሪካዊ
ቦታውን አንዲይዝ ለማድረግ የበኩልዎን አስተዋጵዎ ለማድረግ ይችላሉ ::ECIC Public relations (PR)
We Welcome Your comments, compliments, and complaints! Send Us your Views, Audios, Videos and more. Contact us: E-mail: info@saveethiopians.net.
ኢትዮጵያን
ከጎጂ አምልኮ ቡድኖች
ጥቃት እናድን::
ዜጎች ስለጎጂ አምልኮ ቡድኖች ምንነት ያላቸውን የእውቀት አድማስ ለማስፋት ታስቦ የተሰራ ድረ ገጽ::
